Friday, June 28, 2013

My Heart Beat ( ልቤ ልቤን)


ልቤ ልቤ
 

ፍቅር -
አብረን መሆን እያማረን
አብረን ውለን አብረን አድረን
የፍቅር አምላክ በባርኮቱ - ከምህረቱ ከቸረን
አብረን ኑረን
አብረን ሆነን
ኑረን ኑረን
ኑረን ኑረን - እስክንሞት
ልቤ ተንሰፈሰፈች - መንጥቃ እንዳትሄድ ፈራሁ
ነፍሴም ካንቺ ዘንድ ከርማ - እንዳትዘነጋኝ ስጋት ሰጋሁ

ልቤ በእስትንፋንሴ - ከውስጤም በሚወጣ ወላፈን
እንዳትተን እፈራለሁ- የፍቅር ዋዕይ ሲገርፈን…

ጳዝዮን - ሰኔ 2013


1 comment:

  1. ግና.... የሱን ባርኮት አምነዋለሁ
    ሠዉ መሆን ሠውኛነት ይዞኝ እንጂ ከሠጠኝ እንደማይነሳኝ አምናለሁ
    አየሽ.. ሠው መሆን ክፋቱ ይህ ነው
    ልቤ እንደዛ ተንሰፍስፋ መንጥቃ ለመሄድ ቃታ
    እንዳትዘነጊኝ ከሰጋሁኝ- ሠው መሆን ያልኩሽ ይሄን ነው -እኔም አንችም ስንፈጠር ነፍሳችን ከልባችን ,ልባችን ከነፍሳችን ተያይዛ ተፈጥራለች ወረት ከሚባል ነገር

    ReplyDelete

Leave a Message:

Followers